ሄርኮሉበስ ወይም ቀይ ዓለም
ለሰው ልጅ የሚያስፈልግ መጽሐፍ

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ እያረጋገጥኩት ያለሁት በቅርቡ የሚፈጸመውን ትንቢት ነው፤ ምክንያቱም ስለ ዓለም ፍጻሜ እርግጠኛ ነኝ። አውቀዋለሁ። እያስፈራራሁ ሳይሆን እያስጠነከኩ ነው ምክንያቱም በዚህ ስለምስኪኑ የሰው ልጅ ስለተጨነኩ። እነዚህ ክስተቶች ለመምጣት ረጅም ጊዜ አይፈጁም እና በተሳሳቱ ነገሮች የሚጠፋ ግዜ የለንም። - ቪ.ኤም. ራቦሉ

በሁሉም የዓለም ማዕዘናት፣ ስለ ፍጻሜው ዘመን ሁሉም እርስ በርስ የሚመሳሰሉ ወጎችን እና ትንቢታዊ ገለጻዎችን እናገኛለን።

አብዛኛዎቹ ትንበያዎች በምድር ላይ ስለሚከሰቱት ታላቅ አደጋዎች ያስጠነቅቁናል ለምሳሌ ወደፊት የሚከሰተው የምድር የዋልታ ለውጥ ፣ እርሱ የሚያስከትላቸው የበረዶ ግግር መቅለጥ እና በጠንካራ የመሬት መንቀጥቀጥ እና ሱናሚ ምክንያት ግዙፍ የመሬት ክፍል መጥፋት።

አንድ የሚያመሳስል ነገር የያዙ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ትንቢቶች አሉ ፤ በተለይም በየጊዜው ወደ እኛ ስለሚመጣ ግዙፍ ዓለም ይናገራሉ። ያ ዓለም ቀደም ባሉት ጊዜያት በሌሙሪያ እና በአትላንቲስ የነበሩትን ስልጣኔዎች ለማጥፋት ወደ ስርአተ ጸሃያችን ሳይመጣ አልቀረም ነበር። አሁን፣ ያለንበትን ስልጣኔ በማስቆም አዲስ ዘመን እንዲመጣ ያደርጋል።

በብዙ ትውፊቶች፣ ትንቢቶች እና ቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ባአል ፣ ቀዝቃዛ ዓለም ፣ ቀይ ዓለም ፣ ዎርምዉድ ፣ አጀንጆ ፣ ሄርኮሉበስ፣ ባርናርድ 1ኛ ወዘተ… በሚባሉ የተለያዩ ስሞች ይታወቃል። እንዲህ ዓይነቱ ዓለም ቀድሞውኑ በቴሌስኮፖች የሚታይ ሲሆን መጠኑ ከጁፒተር ስድስት እጥፍ ገደማ ይሆናል።

በህይወት መምጣት እና መሄድ ሁሉም ነገር ወደ መጀመሪያው ወይም ወደ መጨረሻው ይመለሳል። ስለሆነም በቀድሞ ክስተት ሄርኮሉበስ የአትላንቲክ ስልጣኔ እንዲጠፋ አድርጓል። እነዚህ እውነታዎች በሁሉም ሃይማኖቶች እና ባህሎች “ሁለንተናዊ ጎርፍ” ተብለው በትክክል ተተርከዋል።

ብዙ ሰዎች ስለ እንደዚህ ዓይነት የጠፈር ክስተት ተነጋግረዋል። ከመካከላቸው አንዱ የነቃውን የንቃተ ህሊና ችሎታዎችን በመጠቀም የዚያችን ዓለም መምጣት የጠየቀው ቪ.ኤም. ራቦሉ በዚያ ጠፈራዊ አካል ላይ ምርምር እንዲያደርግ አስችሎታል። በአልኪዮኒ ማህበር አማካኝነት በአለም አቀፍ ደረጃ በነጻ የተላከው “ሄርኮሉበስ ወይም ቀይ ዓለም” በተሰኘው ስራው ላይ እንዲህ ሲል ጽፏል።

ሄርኮሉበስ ወደ ምድር ሲቀርብ እና ከፀሐይ ጋር ራሱን ሲያስተካክል ገዳይ ወረርሽኞች በመላው በምድር ላይ መስፋፋት ይጀምራሉ። ሃኪሞችም ሆኑ የወቅቱ ሳይንስ ምን ዓይነት በሽታዎች እንደሆኑ ወይም እንዴት እንደሚፈውሱ አያውቁም። ወረርሽኙን ለመከላከል አቅም የሌላቸው ይሆናሉ።

የጭፍግ እና የጨለማ ጊዜ ይመጣል ፤ የዝግታ መንቀጥቀጥ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ እና ማዕበላት። የዛኔ የሰው ልጅ መብላትና መተኛት ስለማይችል የአዕምሮ ሚዛኑ ይዛነፋል። በአደጋ ወቅት ሙሉ በሙሉ ራሳቸውን በጅምላ እና በእብደት ወደ ዝቅጠት ይወረውራሉ።

ቪ.ኤም. ራቦሉ

ቪ.ኤም. ራቦሉ ታላቁ ኮሎምቢያዊ የኢሶተሪዝም ዘርፍ ተመራማሪ ስለዚያ ስጋት የሰው ልጅን ለማስጠንቀቅ ድምፁን ከፍ አድርጎ ነበር። እንደውም የሥልጣኔያችንና የባህላችን ፍጻሜ ሊያመጣ እንደሚችል ጠቁሟል። በመጽሃፉ ውስጥ የስነ-ልቦና ጉድለቶችን ማስወገጃ ዘዴን እና የአስትራል ፕሮጀክሽን ቴክኒኮች ከመጪው አደጋ ለማምለጥ ያሉን ብቸኛ ቀመሮች እንደሆኑ ያስተምራል።

ቪ.ኤም. ራቦሉ ይህን በማለት ስራውን ያጠቃልላል፡-

ውድ አንባቢ፡- በቁም ነገር የመጀመርን አስፈላጊነት እንድትረዳ ነው በግልፅ እምናገረው። የሚሰራ ሁሉ ከአደጋው ይድናል። ይህ ለአንተ ንድፈ ሃሳቦችን እንድትፈጥር ወይም ውይይት ለማድረግ አይደለም ነገር ግን በዚህ መጽሐፍ ውስጥ እየሰጠሁት ያለውን እውነተኛውን ትምህርት እንድትሮረው እንጂ። ሌላ ምንም ነገር ማድረግ አንችልም።

አልኪዮኒ ማህበር

ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን “ሄርኮሉበስ ወይም ቀይ ዓለም” ሥራን በማሰራጨት እና በማከፋፈል እንደ ወኪል-ተባባሪ ሆኖ ተሾመ።

ደራሲ፡- Joaquín Amórtegui Valbuena (V.M. Rabolú)
አሳታሚ፡- Ángel Prats

አልኪዮኒ ማህበር በሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለው ብሔራዊ የማህበራት መዝገብ ቤት ቡድን 1 ክፍል 1 በብሔራዊ ቁጥር 588698 የተመዘገበ ሲሆን ዋና መሥሪያ ቤቱም በቡርጎስ ከተማ የፖስታ ሳጥን 4 ፣ 09080 (ስፔን) ውስጥ ይገኛል።

ስለ ደራሲው

V.M. Rabolú
ቪ.ኤም. ራቦሉ (ከ1926 እስከ 2000 እ.ኤ.አ)

ቪ.ኤም. ራቦሉ (ከ1926 እስከ 2000 እ.ኤ.አ) ፤ በቶሊማ (ኮሎምቢያ) ተወለደ። እ.ኤ.አ. በ 1952 እውነተኛውን እውቀት አገኘ እናም ለብዙ ዓመታት በኢሶተሪክ ልምምድ አስደናቂ ችሎታዎችን በማዳበር በዓለም ዙሪያ በጣም ታዋቂ የሆነ መንፈሳዊ መመሪያነት በመጨረሻ ለውጦታል።

ወደፊት ስለሚጠብቀን ጊዜ በመገንዘብ የሰው ልጆች የራሳቸውን መንፈሳዊ ዳግም መወለድ ያገኙ ዘንድ ቀመሮችን ለነሱ ለማስተማር ራሱን አጸና። ስለዚህም ከ 1970 ዎቹ ጀምሮ እና ሁል ጊዜም ከራስ ወዳድነት በነጻ መንገድ እውነተኛውን ጥበብ በዓለም አቀፍ ደረጃ በንግግሮች ፣ ኮርሶች እና ኮንግረስ በአደባባይ የማስተማር ጽኑ ስራውን ጀመረ።

እ.ኤ.አ. በ 1998 “ሄርኮሉበስ ወይም ቀይ ዓለም” የተሰኘውን ጽፏል። በእሱ ቀጥተኛ እና ንቁ ልምዱ በመመስረት ቪ.ኤም. ራቦሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ በዓለማችን ላይ የሚፈጸሙትን አስከፊ ክስተቶች ይገልፃል እና ጥልቅ ለውጥ ለማምጣት የሰው ልጅ ሊከተለው የሚችለውን መንገድንም ያብራራል። በአሁኑ ወቅት በሥራው ውስጥ የተካተቱት መግለጫዎች ከ 80 በሚበልጡ አገሮች ውስጥ በአስተምህሮው ተጠቃሚ በሆኑ እጅግ በጣም ብዙ አንባቢዎች እውቅና አግኝተዋል።

ቪ.ኤም. ራቦሉ የነቃ ንቃተ ህሊና ካላቸው ጥቂት ሰዎች አንዱ ነበር። ፍቅረ ንዋይ እና የእሴት እጦት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠፋ ላለው ህብረተሰብ መለያ ምልክቶች በሆኑበት በዚህ ዘመን የእሱ ትምህርቶች አስፈላጊ ናቸው።

ቪ.ኤም. ራቦሉ

ቪ.ኤም. ራቦሉ የነቃ ንቃተ ህሊና ካላቸው ጥቂት ሰዎች አንዱ ነበር። ፍቅረ ንዋይ እና የእሴት እጦት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠፋ ላለው ህብረተሰብ መለያ ምልክቶች በሆኑበት በዚህ ዘመን የእሱ ትምህርቶች አስፈላጊ ናቸው።

ልሳኖች

በዚህ ክፍል ውስጥ ቪ.ኤም ራቦሉ የአስትራል ፕሮጀክሽን ልሳኖችን ሲናገር ማዳመጥ ይችላሉ ትክክለኛውን አባባል እንዲያውቁት።

ፋራኦን

ላ ራ ስ

ከአልኪዮኒ ማህበር ጋር ያለው ትብብር

አልኪዮኒ ማህበር በህጋዊ መንገድ የተመሰረተ ድርጅት ነው። ለትርፍ እንዳልተቋቋመ ድርጅት ሁሉም ተግባሮቹ ምንም አይነት የገንዘብ ትርፍ ሳይኖራቸው በበጎአድራጎት ይከናወናሉ።

የአልኪዮኒ ማህበር “የሄርኮሉበስ ወይም ቀይ ዓለም” መጽሐፍ አሳታሚ ለሆነው አቶ አንጄል ፕራትስ ወኪል-ተባባሪ ሆኖ ይሰራል። ስለዚህም ብቸኛው ዓላማው የዚያ መጽሐፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ማሰራጨት እና ማከፋፈል ነው። በዚህ ምክንያት የአልኪዮን ማኅበር ዋና ተግባር ያንን ሥራ እና ዓለም አቀፋዊ መልእክቱን ያለ ልዩነት ለማሰራጨት የመጽሐፉን ነፃ ቅጂዎች ወደ የትኛውም ቦታ መላክን ያካትታል።

እስካሁን ድረስ ባለው የስርጭት ዘመቻው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አንባቢዎች “ሄርኮሉበስ ወይም ቀይ ዓለም” የተባለውን መጽሐፍ ነፃ ቅጂ እንዲያገኙ አስችሏል። በአሁኑ ጊዜ እና ከቀን ወደ ቀን የትእዛዝ ብዛት ያለማቋረጥ እያደገ ነው። በዚህ ታላቅ ስኬት የተነሳ እራሳችንን በዚህ የስርጭት ዘመቻ ለማስቀጠል ግብ አውጥተናል።

በትእዛዞች ብዛት ምክንያት በአሁኑ ሰዓት እንደየሁኔታው መጽሐፉን በህትመት ወይም በኤሌክትሮኒክስ ፎርማት እንልካለን።

እባካችሁ ይህንን ስራ በማሰራጨት ረገድ የሚከተለውን ቪዲዮ በመጫን እና በኢሜል ለጓደኞች እና ለሚያውቋቸው በመላክ ይርዱን።

ማህበራችንን ማነጋገር ከፈለጉ ወይም ከመፅሃፍ አሳታሚው ጋር የቪ.ኤም. ራቦሉ መጸሃፍ እና መልእክቱን ስርጭትን በተመለከተ ለመተባበር ፍላጎት ካሎት ወይም ከእኛ ጋር የበለጠ ጠንካራ ግንኙነት እና ትብብር እንዲኖርዎት ከፈለጉ ከሚከተሉት አድራሻዎች ውስጥ ወደ ማናቸውም መፃፍ ይችላሉ፡-

በኢሜል ለ፡ [email protected]

በደብዳቤ ለ፡
Alcyone Association
P.O. Box 4, 09080 Burgos (ስፔን)

ነጻ መጸሃፎን ይጠይቁ

ወደብዙ ቋንቋዎች የተተረጎመ።
በመጻፍ ይጠይቁ፡ [email protected]
ወይም የሚከተለውን ቅጽ ይጠቀሙ፡

የማዘዣ ቅጽ

ጥያቄዎን ለማስተዳደር በኮከብ ምልክት (*) ምልክት የተደረገበት ውሂብ መጠየቂያ አስፈላጊ ነው። ይህ መረጃ የሚሰበሰበው እና ጥቅም ላይ የሚውለው የመጽሐፉን የመጠየቂያ ተዛዝ ለማሟላት ብቻ ነው።

መጽሐፉን ለመቀበል ትክክለኛ የኢሜይል አድራሻ ማስገባት አለቦት።

ትዕዛዝዎን ለማስኬድ ይህን ሳጥን ያንብቡ እናም ምልክት ያድርጉበት።

አስገባ የሚለውን ቁልፉ በመጫን ውሂቡን በግላዊነት ፖሊሲ ውል መሰረት በሂደት ውስጥ እንዲያልፍ ተስማምተዋል።